Jump to content

ጎርጎርያን ካሌንዳር

ከውክፔዲያ
የሮማው ፓፓ ግሪጎሪ 8ኛ መቃብር ላይ ፓፓው የካሌንደሩን መጽደቅ አስመልክቶ ሲደሰት የሚያሳይ ቅርጽ

የጎርጎርያን ካለንዳር ወይም በሌላ ስሙ የምዕራቡ ካሌንዳር በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው የቀናት አቆጣጠር ዘዴ ነው። ካሌንደሩን ያስተዋወቀው የሮማው ፓፓ ግሪጎሪ ፰ኛ ነበር። ካሌንደሩ በህዳር 24፣ 1582 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ) የጎርጎርያን ካሌንደር ተብሎ ተሰየመ፣ በአዋጅም ጸና። የአዲሱ ካሌንደር መነሻ ምክንያት የጁሊያን ካሌንደር በአንድ አመት ውስጥ 365.25 ቀንናቶች አሉ ብሎ ያስቀመጠው እምነቱ በ11 ደቂቃወች ከዕውነተኛው የአመት ርዝመት አንሶ መገኘቱ ነበር። ስለዚህም የጁሊያን ካሌንደር ከተሰራ ጀምሮ ፓፓው እስከ ቀየረው ድረስ የተጠራቀመው ስህተት 10ቀን ወጣው። ይህ የ10 ቀን ለውጥ የካቶሊክ ቤ/ክርስቲያናንን የፋሲካ በዓል ስላዛባ ካሌንደሩ መስተካከሉ የግድ ሆነ።